Fana: At a Speed of Life!

የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ለገበታ ለሀገር የ1 ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ቃል ገቡ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ለገበታ ለሀገር የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞትዬስ፥ “ሸገርን በማስዋብ እና እንጦጦ ፓርክ የታየው ድንቅ ስራ ወደ ሌሎችም አካባቢዎች እንዲሰፋ አሻራችንን ለማስቀመጥ በማሰብ ነው ቃል የገባነው” ብለዋል።

በተያያዘ ዜና የጠቅላይ አቃቤ ህግ አመራርና ሰራተኞች የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክትና የእንጦጦ ፓርክን ጎብኝተዋል።

ፕሮጀክቶቹን የጎበኙት አመራርና ሰራተኞቹ በተሰሩት ስራዎች መደነቃቸውን እና ቁርጠኝነቱ ካለ የትኛውንም ፕሮጀክት ማጠናቀቅ እንደሚቻል ማሳያ ነው ብለዋል።

በበእንጦጠ ፓርክና በሸገር ማስዋብ ፕሮጀክቱ ላይ የተሰሩ ስራዎች የራሳቸው ኢትዮጵያዊ ትርጉም ያለቸው መሆኑም ዘመን ተሻጋሪ ያደርጋቸዋል ነው ያሉት።

በድህረ ኮቪድ ቱሪስትን የሚስቡ በመሆናቸው ለተጀመረው የብልፅግና ጉዞ ወሳኝ ናቸው ሲሉም የጠቅላይ አቃቤ ህግ አመራርና ሰራተኞቹ ተናግረዋል።

በሀብታሙ ተክለስላሴ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.