Fana: At a Speed of Life!

የኤጀንሲው መቐለ ቅርንጫፍ ለ47 ጤና ተቋማት መድሀኒትና የህክምና ግብዓቶችን አሰራጨ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ መቐለ ቅርንጫፍ በትግራይ ክልል ለሚገኙ 47 ጤና ተቋማት  18 ሚሊየን ብር የሚያወጣ  የመደበኛ እና የጤና ፕሮግራም መድሀኒትና   የህክምና ግብዓቶችን በቀጥታ በማድረስ ማሰራጨቱ ተገለጸ።

ቅርንጫፉ ለ21 ሆስፒታሎችና 26 ጤና ጣቢያዎች በቀጥታ ያሰራጨ ሲሆን ከእነዚህም መቐለ የሚገኙ 4 ሆስፒታሎች እና ሁሉም ጤና ጣቢያዎች፣ ለውቅሮ፣ ሀውዜን፣ አዲግራት፣ አክሱም ቅድስተ ማርያም፣ ኮረም፣ መኾኒና ሌሎች ሆስፒታሎች ይገኙበታል ።

በሌላ በኩል በሰሜን እና በምዕራብ እንዲሁም በማዕከል ከሚገኙ በኤጀንሲው ቅርንጫፎች የመደበኛ እና የጤና ፕሮግራም መድሀኒት የህክምና ግብዓቶች ለሑመራ፣ አላማጣ እና ለሌሎች ጤና ተቋሟት እየተሰራጨ እንደሚገኝ ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የመቐለ ቅርንጫፍ በአሁኑ ወቅት ከማዕከላዊ መጋዝን ከተላከው 71 ሚሊየን ብር ግምት ካላቸው መድሀኒትና የህክምና ግብዓቶችን ጨምሮ 350 ሚሊየን የሚሆን  የመደበኛ እና የጤና ፕሮግራም መድሀኒትና የህክምና ግብዓቶች ክምችት አለው ተብሏል።

በቅርንጫፉ ከሚገኙ መድሀኒትና የህክምና ግብዓቶቹ ውስጥ ለእናቶች እና ህፃናት ጤና፣ ለስኳርና ደም ግፊት ህመምተኛች፣ ለፀረ ወባ፣ ለሳንባ ነቀርሳ እና ኤች አይቪ ኤድስን ለማከም የሚውሉ ናቸው ተብሏል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.