Fana: At a Speed of Life!

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር በጋዛ የሚደረገው ጥቃት እንደሚቀጥል አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጋዛ የሚደረገው ጥቃት እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡
ፍልስጤማውያን የእስራኤል ወታደሮች በአል አቅሳ መስጊድ ገብተው ወስደውታል ያሉትን እርምጃ ተከትሎ የተጀመረው ግጭት የበርካቶች ህይወት እንዲልፍ እና የአካል ጉዳት እንዲደርስ እያደረገ ይገኛል፡፡
ዛሬ ማለዳም እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ባደረሰችው የአየር ድብደባ 33 ፍልስጤማውያን የተገደሉ ሲሆን ከ10 በላይ ሰዎች ቆስለዋል፡፡
በአጠቃላይም በጋዛ ሰርጥ ባለፈው ሳምንት ብቻ 180 ሰዎች ለህልፈት የተዳረጉ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 52ቱ ሕፃናት መሆናቸው ታውቋል፡፡
ከ 1 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቆስለዋል ነው የተባለው ፡፡
በእስራኤል በኩልም ሁለት ህፃናትን ጨምሮ 10 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጋዛ ላይ የሚደረገው ጥቃት እንደአስፈላጊነቱ እንደሚቀጥልና እስራኤል ከጋዛ ለሚወነጨፈው ሮኬት ምላሽ መስጠቷን እንደምትቀጥል አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ፡-አልጀዚራ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.