Fana: At a Speed of Life!

የእስራኤል መንግስት ለተፈናቀሉ ዜጎች የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል መንግስትና ህዝብ በግጭቱ ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች 14 ቶን የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ፡፡

የእስራኤል መንግስት በአሸባሪውና ወራሪው ህወሓት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቀለው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎችና በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የሚሆን ግምቱ 14 ቶን የሆነ የንጽህና መጠበቂያ፣ ክራንች፣ ዊልቼርና የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ለሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስርክቧል፡፡

በርክክብ ስነስርአቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፥ የእስራኤል መንግስትና ህዝብ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ድጋፉ የሁለቱን ሀገራት የቆየ ታሪካዊ ወዳጅነት ከፍ ከማድረጉም በላይ በቀጣይ የሚኖረውን የላቀ ትብብርና ወንድማማችነት ይበልጥ እንዲጠናከር እንደሚያደርገው ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ በበኩላቸው፥ የተደረገው ድጋፍ ከህዝብ ለህዝብ የተደረገ መሆኑንና የእስራኤል መንግስት በኢትዮጵያ በተለያዩ ችግር ውስጥ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በማህበራዊና በጤና ዘርፎች እያደረገ የሚገኘውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.