Fana: At a Speed of Life!

የእስራኤል የማዕድን ኩባንያ በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ሥራውን ለማቀጠል ያለውን ቁርጠኝነት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ዋና መስሪያ ቤቱ በእስራኤል የሆነው ሌካ የተባለው በማዕድን ዘርፍ የተሰማራው ኩባንያ የሥራ ኃላፊዎች በዛሬው እለት ከማዕድን ሚኒስትር ታከለ ኡማ ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡

በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር ÷ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አመራር መንግስት ብልጽግናን በሀገራችን ለማስፈን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃዎችን በቁርጠኝነት ሲወስድ መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ በፈተና ላይ በምትገኝበት በዚህ ወቅት በግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢንጅነር ታከለ ÷ “የእስራኤል የማዕድን ኩባንያዎች በዚህ ወሳኝ ወቅት ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ጎን ለእውነት ወግናችሁ ስለቆማችሁ ምስጋና ይገባቸኋል” ብለዋል፡፡

በስብሰባው የተገኙት በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ረታ ዓለሙ ÷ በኢትዮጵያ በማዕድን ልማት ላይ የተሰማሩ የእስራኤል ማዕድን ኩባንያዎችን ተወካዮች በዘርፉ የሚያርጉት እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የኩባንያዎቹ ኃላፊዎች በዚህ ወሳኝ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን እንደሚቆሙ የገለፁ ሲሆን ÷ ስራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡

አምባሳደር ረታ ÷ ኢትዮጵያ እና እስራኤል ጠንካራ ታሪካዊ እና መንፈሳዊ ትስስር ያላቸው መሆኑን ጠቁመው ÷ የግሉ ዘርፍ ኢንቨስትመንት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማጠናከር ትልቅ አስተዋፅዖ ማበርከት እንደሚችል ማስታወቃቸውን ከእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.