Fana: At a Speed of Life!

የእነ አቶ ጃዋርን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ፍርድ ቤቱ በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የእነ አቶ ጃዋር መሀመድን የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ፍርድ ቤቱ በድጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የህገ መንግስትና የጸረ ሽብር ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ዛሬ በሰጠው ቀጠሮ መሰረት ተሰይሞ የነበረው የተጠርጣሪዎችን የእምነት ክህደት ቃል ለመመልክት ነበር።

ይሁንና ተከሳሾቹ  ቤተሰቦቻቸን ችሎት ስላልታደሙ የእምነት ክህደት ቃላቸንን  መስጠት አንችልም ሲሉ አቤቱታ አሰምተዋል።

አቃቢ ህግም ጊዜው በተገፋ ቁጥር የተከሳሾችም ሆነ የኛንም ጊዜ እየተወሰደ ይሄዳል ስለዚህ ጊዜው ታሳቢ ቢደረግ ሲል አስተያየቱን  ሰጥቷል።

አቶ ጃዋርም የፍርድ ቤቱን ጊዜ ለመውስድ አይደለም ቤተሰቦቻችን መግባት ስላለባቸው ነው ሲሉ በፍርድ ቤቱ ያላቸውን እምነት  ጥሩ እንደሆነ ገልጸዋል።

አቤቱታውን ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ለመመልከት ለጥር 27 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.