Fana: At a Speed of Life!

የእናቶችን ሞት 50 በመቶ ለመቀነስ እየተሰራ ነው – ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የእናቶችን ሞት 50 በመቶ ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

‘ኮቪድ-19 በእናቶችና በልጆችና በወጣቶች ስነ ተዋልዶ ጤና አጠባበቅ ላይ ያደረሰው ተጽዕኖ’ በሚል መሪ ሀሳብ 29ኛው የኢትዮጵያ የፅንስና የማኅፀን ሐኪሞች ማኅበር አመታዊ ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው።

በዚህ ወቅት የጤና ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ ፤ ኮቪድ-19 መከሰት በስነ ተዋልዶ ጤና አጠባበቅ ላይ ሰፊ ተጽዕኖ አሳድሮ ነበር ተናግረዋል።

ወረርሽኙን ለመከላከል በተከናወነው ሰፊ እንቅስቃሴ በሽታውን ከመከላከል አልፎ የስነ ተዋልዶ ጤና አጠባበቅ ላይ የተከሰቱ ችግሮችን ለመቅረፍ ተችሏል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የፅንስና የማኅፀን ሐኪሞች ማኅበርም በዚህ ረገድ ትልቅ ድርሻ እንደነበረውና የእናቶችን ሞት በመቀነስ ረገድ ሰፊ ስራ ማከናወኑን ገልጸዋል።

ማኅበሩ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ በሕክምና፣ በአቅም ግንባታ እና ግንዛቤ በማስጨበጥ ያከናወናቸውን ሰፊ ስራዎች አጠናከሮ እንዲቀጥል አመልክተዋል።

ጤና ሚኒስቴርም የእናቶችን ሞት 50 በመቶ ለመቀነስ እየሰራ እንደሚገኝ ዶክተር ደረጄ አስታውቀዋል።

ይህንንም ለማሳካት በቤተሰብ ምጣኔ እቅድ ላይ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸው፤ በስነ ተዋልዶ ጤና ላይ የሚሰሩ የመንግሥትና የግል የጤና ተቋማት ተመሳሳይ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት አብሮ መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችም ኮቪድ-19 በእናቶችና በልጆችና በወጣቶች ስነ ተዋልዶ ጤና አጠባበቅ ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽዕኖ ጥናት በመስራት መፍትሔ ማፈላለግ እንደሚገባቸው ነው ያመለከቱት።

በመድረኩ አለም አቀፍ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ኮቪድ-19 በእናቶችና በልጆችና በወጣቶች ስነ ተዋልዶ ጤና ላይ ያደረሰውን ተጽዕኖና ዘርፉን የተመለከቱ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች እንደሚቀርቡ ታውቋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.