Fana: At a Speed of Life!

የእንግሊዛዊቷ የሳራ ኤቨራርድ ገዳይ ፖሊስ ዌይን ኩውዝንስ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሣራ ኤቨራርድን የገደላት  ፖሊስ መኮንን በቁጥጥር ስር ዉሎ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበታል።

ዋይኔ ኩውዝንስ የተባለዉ የ48 አመት ጎልማሳ የፖሊስ መኮነን የ33 አመቷን ወጣት በክላፋም ውስጥ ከሚገኘው የጓደኛዋ ቤት ወደ ቤቷ ስትመለስ መጋቢት ወር ላይ ነበር ጠለፋዉን የፈጸመዉ፡፡

በ48 አመቱ ጎልማሳ የተፈጸመዉን የጠለፋና የአስገድዶ መድፈር እንዲሁም ግድያ ወንጀል በእለቱ ተሰይመዉ ፍርድ የሰጡት ዳኛ ፉልፎርድ በጣም አሰቃቂ ፣አሳዛኝና ሙሉ በሙሉ ጭቃኔ የተሞላበት ነዉ ብለዉታል፡፡

ይህም ጭካኔ የተሞላበት ድርብርብ ወንጀል በመሆኑና ጉዳዩ ከተራ የግድያ ወንጀል የዘለለ እና ከሽብር ወንጀል ጋር እንዲስተካከል የሚያደረገዉ ደግሞ ግለሰቡ የፖሊስ መኮነንነት ሚናዉን ያላግባብ መጠቀሙ ሲሆን ÷ ዜጎች ለጸጥታ አስከባሪ ያላቸዉን እምነት እንዲያጡም የሚያደረግ በመሆኑ የዕድሜ ልክ እስራት ሊያስቀጣዉ እንደቻለም ዳኛ ፉልፎርድ ለችሎቱ አስረድተዋል፡፡

ምንጭ ፡- ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.