Fana: At a Speed of Life!

የእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንጦጦ ፓርክ በይፋ ተመረቀ፡፡

ፓርኩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መርቀው ከፍተውታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ በፓርኩ በተለያዩ የስራ መስኮች ለተሰማሩ ድርጅቶች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው በዚህ ስፍራ ውብ መንደር እንዲሠራ ያደረጋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን ለመቀየር የሚስፈልገው ትብብር መሆኑንም አንስተዋል፡፡

ለአንድ እራት 5 ሚሊየን ብር በመስጠት ላመኑን ባለሀብቶች ምስጋና ይድረሳቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ባለሃብቶች ለገበታ ሸገር ያደረጉት አስተዋጽዖ ፍሬ ስላፈራ ወደ ገበታ ለሀገር እንዲሸጋገሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአዲስ አበባ በሂልተን እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መካከል ያለው የተዘጋ ቦታም ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆንም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በፓርኩ የስራ እድል የተፈጠረላቸው ከ460 በላይ በአካባቢው የሚገኙ እናቶችም የስራ መስሪያ ቦታቸውን ቁልፍ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ተረክበዋል፡፡

በፓርኩ ውስጥ የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በልዩ ልዩ መንገድ መስዋዕትነት ለከፈሉ የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች የእውቅና ሃውልት ቆሞላቸዋል፡፡

ሸገርን ማስዋብ” ፕሮጀክት አካል የሆነው የእንጦጦ ፓርክ ሃገርኛ ስያሜዎችን እና መዝናኛ ዘርፎችን ባካተተ መንገድ የተገነባ ሲሆን ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠሩም ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.