Fana: At a Speed of Life!

የኦሚክሮን ክትባትን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ቤተ ሙከራዎች እየተደረጉ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የኦሚክሮን  የኮሮና ቫይረሰ ክትባትን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የተለያዩ የቤተ ሙከራ ሂደቶች እየተከናወኑ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በቅርቡ ይፋ የተደረገው የኦሚክሮን ክትባትን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ቤተ ሙከራዎች በመካሔድ ላይ ሲሆኑ ውጤታቸውም÷ በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እስካሁን ይፋ ከተደረጉት ክትባቶች ዴልታ ቫሪያንት ጥቅም ላይ በመዋል ቀዳሚውን ስፍራ  መያዙን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ዴልታ ቫሪያንት ከአልፋ፣ ቤታ እና ጋማ ከተባሉ ክትባቶች በተሻለ ሁኔታ የመከላከል አቅም እንዳለው ነው ባለሙያዎች የሚናገሩት።

ፒ ፋይዘር፣ ጆንሰን እና ጆንሰን እና ሞደርና የተባሉ ክትባቶቸ ከኦሚክሮን ክትባት ጋር በሚመሳሰሉ ስሪቶች እየተቀመሙ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

የአሜሪካዉ መድሃኒት አቅራቢ ድረጅት ፒ ፋይዘር በ100 ቀናት ውስጥ አዲስ ክትባት ይፋ እንደሚያደርግ ቃል የገባ ሲሆን÷ይሁን እንጂ መድሃኒቱን ቀምሞ ለመጨረስ  ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል ተነግሯል፡፡

 

ምንጭ÷ ቲ አር ቲ ወርልድ

 

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

 

መከላከያን ይደግፉ!

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.