Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ባለፈው በጀት አመት ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ባለፈው በጀት አመት ከ1.4 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ገለፀ፡፡
ባንኩ 16ኛ የባለአክሲዮኖች አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ እና 9ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በአዳማ እያካሄደ ይገኛል።
የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በ2012 በጀት አመት 1 ቢሊዮን 423 ሚሊዮን ብር አጠቃላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ፍቅሩ ደሲሳ ያለፈውን አመት ተቀማጭ ገንዘቡ 45.51 ቢሊዮን ብር ደርሷል ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ባንኩ በመላ ሀገሪቱ 420 ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን በሀገሪቱ ከሚገኙ የግል ባንኮች 3ኛ ደረጃ መያዙንን ገልፀዋል።
በረጋሳ ፍሮምሳ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.