Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ እና የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በልማት እና በሰላም እየመከሩ  ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ እና የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በጋራ ልማት እና ሰላም ጉዳዮች ላይ  እየመከሩ ነዉ፡፡

በምክክር መድረኩ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በተደጋጋሚ የሚከሰቱ የሰላም እና የጸጥታ ችግሮችን ተቀናጅቶ ለመከላከል በትብብር መስራት የሚቻልበት ሁኔታ ልዩ ትኩረት መሰጠቱም ነው የተገለጸው፡፡

በሁለቱም ክልሎች የሚፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን ተከትሎ በንጹሃን ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለዉን ሞትና መፈናቀል በፍጥነት ማስቆም፣ የግጭቱ ጠንሳሾች እና ተዋናዮች ላይ አስፈላጊዉን እርምጃ መዉሰድ፣ በተከሰቱ ግጭቶች ጉዳት የደረሰባቸዉ ወገኖች ፍትሕ እንዲያገኙ እና ወንጀለኞች ለሕግ እንዲቀረቡ ማድረግ፣ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀያቸው በፍጥነት መመለስና ማቋቋም እንዲሁም በክልሎቹ ዘላቂ ሰላም ከማስፈን አኳያ በትብብር ለመሥራት  በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሁለቱ ክልሎች አመራሮች በመወያየት ላይ ይገኛሉ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የኦሮሞ እና የአማራ ወንድማማች ሕዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ትስስርና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማጠናከር፣ አጎራባች ዞኖች ላይ አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ግጭቶችን በተቀናጀ ሁኔታ መከላከል፣ በሁለቱ ክልሎች መካከል እየተሠሩ ያሉ የመሰረተ ልማት ሥራዎችን በፍጥነት  በማጠናቀቅ የሕዝቦችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የዉይይቱ አንኳር ጉዳዮች  መሆናቸውን አብመድ ዘግቧል።

በመድረኩ የሁለቱም ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን÷ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በጋራ እየመሩት ነዉ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.