Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል መንግስትና የብልፅግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ የ2012 አፈጻፀምና የ2013 እቅድ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል መንግስትና የብልፅግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ የ2012 አፈጻፀም ግምገማ እና የ2013 እቅድ የውይይት መድረክ እየተካሄ ነው።

የ2012 አፈጻፀም ግምገማ እና የ2013 እቅድ የውይይት መድረኩ በአዳማ ከተማ ነው በመካሄድ ላይ የሚገኘው።

የውይይት መድረኩ ላይም የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከዞን እስከ ወረዳ ያሉ የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግርም፥ በ2012 በጀት ዓመት የተሰሩ ስራዎች ጥሩ መሆናቸውን አንስተዋል።

ሆኖም ግን አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮች ተቀርፈው ሌሎች የልማት ስራዎች በትኩረት እንዲሰሩ የፀጥታ አካላት ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስታውቅዋል።

የኦሮሞ ህዝብ ሰላምና ልማትን ነው የሚፈልገው ያሉት አቶ ሽመልስ፥ ሆኖም ግን በተለመደው መልኩ በመጓዝ ህዝቡ ለልማት ያለውን ፍላጎት ማሟላት ስለማይቻል የህዝቡን ተሳትፎ በማጠናከር በቁርጠኝነት መስራት እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል።

በየትኛውም ችግር ውስጥ የተጀመረው የብልፅግና ጎዳና በህረተሰቡ ተሳትፎ እንደሚሳካም ነው አቶ ሽመልስ የተናገሩት።

የብልፅግና ፓርቲ የኦሮሚያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በበኩላቸው፥ በስራ ላይ ያጋጠሙ ጥንካሬዎችና ድክመቶች በመለየት፤ ጥንካሬዎች እንዲቀጥሉ፤ የተለዩ ድክመቶች ደግሞ እንዲስተካከሉ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በዛሬው እለት በአዳማ ከተማ የተጀመረው የኦሮሚያ ክልል መንግስትና የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የውይይት መድረክ የ2012 በጀት ዓመት አፈፃፀምን ከገመገመ በኋላ የ2013 በጀት ዓመት እቅድ ላይ በመወያየት ከመግባባት በመድረስ እንደሚጠናቀቅም ይጠበቃል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.