Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል መንግስት የክልሉን ሠላም በማረጋገጥ ሂደት የላቀ ሚና ለተጫወቱ የፀጥታ አካላት የዕውቅና ስነ ስርዓት እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የከልሉን ሠላም በዘላቂነት በማረጋገጥ ሂደት የላቀ ሚና ለነበራቸው የፀጥታ አካላት እውቅና ሰጥቷል ።

የዕውቅና ስነስርዓቱ በአዳማ ገልማ በአባ ገዳ አዳራሽ እየተካሄደ መው የሚገኘው፡፡

በስነስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የእውቅና ስነ ስርዓቱ የላቀ አፈፃፀም ለነበራቸው ፖሊሶች የማዕረግ እድገት መስጠትን ይጨምራል ተብሏል ።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አራርሳ መርዳሳ የክልሉ ፖሊስ አሁን የተገኘውን ሰላም ይበልጥ ለማረጋገጥ ከመቼው ጊዜ በላቀ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን በስነ ስርዓቱ ላይ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.