Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል መንግስት የ2015 ረቂቅ በጀት ከ158 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ሆኖ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን አካሂዶ ለ2015 በጀት ዓመት የክልል መንግስት በጀት 158 ቢሊየን 629 ሚሊየን 503 ሺህ 205 ብር ሆኖ እንዲጸድቅ ለጨፌው መርቷል፡፡

ምክር ቤቱ ለመደበኛ ወጪ 28 ቢሊየን 699 ሚሊየን ብር፣ ለካፒታል ወጪ ደግሞ 38 ቢሊየን 140 ሚሊየን ብር መድቧል፡፡

በተጨማሪም በክልሉ ለሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ የሚውል 91 ቢሊየን 189 ሚሊየን ብር የተጠየቀ ሲሆን፥ ለአካባቢ ጥበቃ ደግሞ 600 ሚሊየን ብር እንደሚያስፈልግ ተመልክቷል፡፡

የክልሉ መንግስት በጀት የሚሸፈነው ከፌደራል መንግስት በሚገኝ ድጋፍ እና በክልሉ ከተለያዩ ምንጮች ከሚገኝ ገቢ መሆኑም እንደተመለከተ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነውመረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.