Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ድጋፍ ሲያደርጉ ለነበሩ አካላት እውቅና ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ በትምህርት ልማት ዘርፍ በተለያያ መልኩ ድጋፍ ሲያደርጉ ለነበሩ ተቋማት እና ግለሰቦች የእውቅና አሰጣጥ መርሀግብር አካሂዷል።

በአዳማ ከተማ ገልመ አባ ገዳ የተካሄደው መርሀግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ።

በመርሀግብሩም እውቅና የተሰጣቸው ለትምህርት ሴክተሩ በተለያያ መልኩ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ዩኒቨርሲቲዎች ፣ ባለሀብቶች ፣ መምህራን ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች እንዲሁም የተሻለ አፈፃፀምን ያስመዘገቡ ዞኖችና ወረዳዎች ናቸው።

በክልሉ የትምህርት ልማት ስራው ውጤታማ እንዲሆንም የህዝቡ ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበረ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ ገልፀው፤ በዚህም ከህብረተሰቡ በተለያየ መልኩ ከ5ነጥብ2 ቢሊየን ብር በላይ ድጋፍ መደረጉን አንስተዋል።

በትምህርት ልማት ዘርፉ በህብረተሰቡ ተሳትፎ ተጨማሪ ከ34ሺ 200 በላይ የመማሪያ ክፍሎች፣ ከ3ሺበላይ ተጨማሪ ቤተመፃህፍትና ከ1ነጥብ2 ሚሊየን በላይ መጻህፍት ማሰባሰብ መቻሉ ተገልጿል ።

በክልሉ በዘንድሮ ዓመት በተጀመረው ኢፈ ቦሩ ፕሮጀክትም 7አዳሪ ፣100ሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም 40 ልዩ ት/ቤቶች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ግንባታቸው እየተከናወነ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ አሁን ላይም አፈፃፀሙ 30በመቶ መድረሱ እና የክልሉ መንግስት ለፕሮጀክቱ 4ነጥብ 9 ቢሊየን ብር መመደቡ ተገልጿል ።

በተጨማሪም ባለፈው የክረምት ወራት ብቻ በበጎ ፈቃድ 34 ሺ 200 በላይ ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል።
ይህም 5 ቢሊዮን ብር የሚገመት መሆኑ ተገልጿል።

በትዝታ ደሳለኝ እና ረጋሳ ፍሮምሳ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.