Fana: At a Speed of Life!

የከረዩ አባገዳ በሸኔ መገደላቸውን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከረዩ አባገዳ ከድር ሀዋስ ቦሩ በሸብርተኛው ሸኔ መገደላቸውን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለፀ፡፡
በከረዩ አባገዳ ላይ በአሸባሪው ሸኔ በተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የተሰማውን ሀዘን ይገልፃልም ብሏል መግለጫው፡፡
የሽብር ቡድኑ በየቀኑ ንፁሃንን በአሰቃቂ ሁኔታ እየገደለ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያለውን ጭካኔ እያረጋገጠ ይገኛልም ነው ያለው፡፡
ሸኔ ሽማግሌዎችን፣አባገዳዎችን ፣ሀደ ስንቄዎችን እየገደለና ክብር እያሳጣ መሆኑን ቢሮው ገልጿል፡፡
የሽብር ቡድኑ ከዚህ በፊትም በጉጂ ዞን በአካባቢው ማህበረሰብ የሚወደዱና የሚከበሩ የሃገር ሽማግሌ የሆኑትን ሃጂ ዑመር ዋጫሌን በአሰቃቂ ሆኔታ በመግደል ጨካኝነቱን አሳይቷል ነው ያለው፡፡
ሸብርተኛው ሸኔ ዓላማው በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የኦሮሞ ህዝብን አንገት ማስደፋት ነው ያለው መግለጫው አሸባሪውን ሕወሓትን ጨምሮ የሽብር ቡድኖቹ የመቀበሪያ ጊዜያቸው በመቅረቡ ተስፋ በመቁረጥ ጨካኝ ርምጃ ህዝቡ ላይ እየወሰዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የክልሉ ህዝብም ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆኑ ተላላኪውንና የኦሮሞን ህዝብ ለማዋረድ ቀን ከሌሊት የሚሰራውን የሽብር ቡድን ለመደምሰስ ሁለገብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.