Fana: At a Speed of Life!

የከተማዋን ገቢ ለማሳደግ ቅንጅታዊ  አሰራር ለመፍጠር ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 16 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ለመፍጠር ያለመ ውይይ ተካሂዷል።

የምክክር መድረኩን   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ   ያዘጋጀው ሲሆን÷ ውይይቱም ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን ለማጠናከር  ያለመ  መሆኑ ተመላክቷል።

በውይይቱም በመዲናዋ የሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር አለመኖር ከተማዋ የምታመነጨውን ገቢ በአግባቡ ለመሰብሰብና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ላይ ችግር እንደሚኖረው ተገልጿል ።

በመሆኑም ይህንን ችግር ለመፍታት እና የከተማዋን ገቢ ለማሳደግ የሚያስችል  ቅንጅታዊ አሰራር መፍጠር ወሳኝ መሆኑን በውይይቱ ተነስቷል።

በዚህም ገቢን ለማሳደግና አገልግሎት ጥራት ለማሻሻል ፣  በታክስ አሰባሰብ ረገድ እያጋጠሙ ያሉ የታክስ ማጭበርበርና የግብር ስወራ ተግባራት በተደራጀ እና በተቀናጀ አኳኋን በአብሮነት በመስራት ከተማዋ  ልታገኘው የሚገባትን ገቢ መሰብሰብ የሚቻልባቸው ሁኔታዎች ምክክር ተካሂዷል፡፡

በሲሳይ ወርቁ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.