Fana: At a Speed of Life!

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ትናንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔዎችን አሳልፏል ።

በዚሁ መሰረት ፦

1- የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ለታካሚ ህፃናት እና ቤተሰቦች ስቃይን ለመቀነስ በነፃ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የበጎ አድራጎት ስራ በዘላቂነት ለመደገፍ ያስችል ዘንድ የታክስ የዕዳ ምህረትና ከኪራይ ገቢ ግብር ነፃ እንዲደረግ ካቢኔው ወስኗል ።

2- በከተማዋ ለሚገኙ ዝቅተኛ የተማሪዎች የምገባ ስራ ላይ ለተሰማሩ እናቶች የአንድ አመት የገቢ ግብር ወጪን የዕዳ ምህረት እንዲደረግም ውሳኔ ተላልፏል

3. በመጨረሻም ከተማ አስተዳደሩ ለቢሮ አገልግሎት በአመት 746 ሚሊዮን ብር በላይ የኪራይ ወጪ የሚያወጣባቸውና እነዚህ ቢሮዎች በተበታተኑ ቦታዎች በመሆናቸው ለተገልጋይ ከፍተኛ እንግልትን እና የህዝብ ገንዘብ ብክነት እያስከተለ ስለሆነ እነዚህ ቢሮዎች ሁሉንም ሰብሰብ አድርጎ በሁለት ክላስተር ለተገልጋዮች ለአገልግሎት ምቹ እና ወጪ ቆጣቢ የሚሆኑ ቢሮዎች ግንባታ ፕሮጀክት እንዲጀመር መወሰኑን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሰክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.