Fana: At a Speed of Life!

የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ ተገብቷል- የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው የከተራና የጥምቀት በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስራው ስኬታማነት እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
ኮሚሽኑ በዓላቱ በሰላም ተጀምረው እንዲጠናቀቁ ለወንጀል እና ትራፊክ አደጋ መከላከል ተግባሩ ልዩ ትኩረት በመስጠት በርካታ የሰው ኃይል ማሰማራቱን ገልፆ በታቦት ማደሪያ ስፍራዎች በተለይም በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች በሚገኙበት ጃን ሜዳ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ ተከፍቶ አግልጋሎት እንደሚሰጥም ተገልጿል፡፡
ኮሚሽኑ ከበዓሉ መንፈስና ከህገ-መንግስቱ እንዲሁም ከህግ ጋር የሚቃረኑ የሌላን ወገን መብት የሚጋፉ መልዕክቶችም ሆኑ ድርጊቶች ፍፁም ተቀባይነት እንደሌላቸውና ይህን ሲፈፅሙ በሚገኙ ላይ በህግ አግባብ እርምጃ እንደሚወስድም አስታውቋል፡፡
ርችት መተኮስ ለፀረ-ሰላም ኃይሎች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር በመሆኑም ርችት መተኮስ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ገልጿል፡፡
በዓሉ በሚከበርበት ስፍራ ምንም አይነት የጦር መሳሪያ፣ ተቀጣጣይም ሆነ ስለት ነገሮችን ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል እንደሆነ የበዓሉ ታዳሚዎች ተገንዝበው ለፍተሻ ትብብር እንዲያደርጉ እንዲሁም በዓሉ በሰላም እንዳይከበር አንዳንድ ፀረ-ሰላም ኃይሎች የብሔር ግጭት ለማስነሳት እንደሚንቀሳቀሱ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
ታቦታት በሚያልፉበት ወቅትም አሽከርካሪዎች የፀጥታ አካላት ለሚሰጧቸው ተዕዛዝ የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪው አቅርቧል፡፡
ህብረተሰቡ በማንኛው ወቅት ከፀጥታ ስራ ጋር ተያያዥ እና አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙትም ይሁን ጥቆማ ለመስጠት እንዲሁም የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘት በስልክ ቁጥር 01-11-26-43-77 ፣ 01-11-26-43-59 ፣ 01-18-27-41-51 ፣ 01-11-11-01-11 እና በ991 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም ይቻላልም ነው ያለው፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.