Fana: At a Speed of Life!

የከንቲባዎች ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የከንቲባዎች ፎረም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡
 
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከንቲባዎቹ በከተማዋ የተገነቡና እየተገነቡ የሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶችን መጎብኘታቸው በየአካባቢው ያለውን ፀጋ ወደ ሀገራዊ ጥቅም ለመቀየር ያግዛል ብለዋል፡፡
 
ጉብኝቱ ከንቲባዎቹ በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ከተጠናቀቁና እየተጠናቀቁ ከሚገኙ ግዙፍ የልማት ግንባታዎች የፕሮጀክት አፈጻጸም ተሞክሮዎችን መውሰድ እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
 
በዚህም መስቀል አደባባይ ፊትለፊት ስለተገነባው የኪነ-ህንጻና የከተማ ማዕከል እንዲሁም ስለመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት አፈጻጸም ምክትል ከንቲባዋ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡
 
ከንቲባዎቹ የአዲስ ሆል የስነ ህንጻ ማዕከል፣ የመስቀል አደባባይ ፕሮጀክት እና የእንስራ የሸክላ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡
 
በጉብኝታቸው ወቅትም በእንስራ የሸክላ ማዕከል ከተሰሩ ባህላዊ ሽክላዎች ለከንቲባዎቹ በስጦታ ተበርክቷል፡፡
 
ከንቲባዎቹ የእንጦጦ እና የሸገር ፓርኮችን ጨምሮ አምስት ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡
 
በሶዶ ለማ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.