Fana: At a Speed of Life!

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለምርምርና ለቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ፖሊሲውን በማጠናከር ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምርና በቴክኖሎጂ ፈጠራ እገዛ ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
30ኛው ሀገር አቀፍ የምርምር ጉባኤ ”ምርምር የማህበረሰብ አገልግሎትና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ለመልሶ መቋቋምና ዕድገት’’ በሚል መሪ ቃል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር በለጠ ሞላ በጉባኤው መክፈቻ ላይ÷ ”ተለዋዋጭ የሆነው የአለም ኢኮኖሚ በሀገራችን ላይ የሚያሳድረውን ተፅእኖ ለመቋቋም በጥናትና ምርምር የተደገፈ የኢኮኖሚ ፖሊሲና ስትራቴጂ ወሳኝ ሚና አለው” ብለዋል።
የሀገሪቱን የቴክኖሎጂ ሽግግርና ፈጠራ ለማጠናከር የሚያግዙ ስትራቴጂና ፖሊሲዎችን በመንደፍ ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው÷ በአለም አቀፉ ዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ተወዳዳሪ ለመሆን እንዲቻል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምርና በቴክኖሎጂ ሽግግር የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አመልክተዋል።
የጎንደር የዩኒቨርሲቲ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ቢኒያም ጫቅሉ÷ በምርምር ጉባኤው ከ100 በላይ የምርምር ስራዎችና ከ20 በላይ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶች ይቀርባሉ ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.