Fana: At a Speed of Life!

የኪዳን መረዳጃ እድር ማኅበር 1 ሚሊየን ብር የሚገመት የአልባሳት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መሰከረም 23፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በአዲስ አበባ የሚኖሩ የኪዳን መረዳጃ እድር ማኅበር በደባርቅና ዳባት ወረዳ በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 1 ሚሊየን ብር የሚገመት የአልባሳት ድጋፍ አደረገ፡፡

የማኅበሩ አባላት በጭና ተገኝተው ነው ጉዳት ለደረሰባቸው ተጎጅዎች የአልባሳት ድጋፍ ያስረከቡት፡፡

የመረዳጃ እድር ማኅበሩ 625 ብርድ ልብስና የተለያዩ አልባሳትን ያካተተ ድጋፍ ነው ለተጎዱ ወገኖች ያበረከቱት።

የማህበሩ አባላት በደባርቅ ወረዳ ቦዛ ቀበሌ ተገኝተው ተጎጅ ወገኖችን እንደሚመለከቱና ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያስረክቡም መገለፁን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ የኪዳን መረዳጃ እድር ማኅበር ምክትል ሊቀመንበር አቶ አበባው ተቀባ ÷ አሸባሪው የትህነግ ቡድን በንጹሐኖች ላይ የፈፀመው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በየትኛውም ዓለም አልተፈፀመም ብለዋል፡፡

በድጋፍ ርክክቡ የተገኙት የዳባት ወረዳ አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ተወካይ ኀላፊ አቶ ሙሉቀን ፀጋነው በአዲስ አበባ የሚኖሩ የኪዳን መረዳጃ እድር ማኅበር አባላት ለወገኖቻቸው ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል።

በቀጣይ ድጋፍ የሚያደርግ ማንኛውም አካል የዕለት ደራሽ ምግብ፣ የቤት ቁሳቁስና መሰል ድጋፎችን ቢያመጡ የተሻለ መሆኑም ጠቁመው የኅብረተሰቡ ንብረት በመዘረፉና አዝመራውም በመውደሙ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ተጠይቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.