Fana: At a Speed of Life!

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 29 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ ወቅት በሀገራቱ መካከል ሊኖር በሚችለው የኢንቨስትመንት እና ሌሎች የኢኮኖሚ ትብብሮች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋርም የካናዳ ባለሀብቶችም አብረው አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፥ በነገው እለት በሚካሄደው የቢዝነስ ፎረም ይካፈላሉ ተብሎም ነው የሚጠበቀው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፈረንጆቹ የካቲት 6 ጀምረው እስከ የካቲት 14 ቀን 2020 በሚቆየው ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ወደ ሴኔጋል ያቀናሉ።

በጉብኝታቸው ወቅትም በየሀገራቱ በሚኖራቸው ቆይታ የኢኮኖሚ እድልና ብልፅግና፣ የዓየር ንብረት ለውጥ፣ ዴሞክራሲ እና የሴቶች እኩልነት ጉዳዮችን አብይ አጀንዳቸው ያደርጋሉ ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት በአዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር እንደሚወያዩ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.