Fana: At a Speed of Life!

የኬንያ ንግድ ምክር ቤት ከኢትዮጵያ ጋር የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስርን  ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሪቻርድ ንጋትያ እና  ሌሎች የስራ  ኃላፊዎች  በኬንያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሃላፊ ከአምባሳደር ሲራጅ ረሺድ ጋር  ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱ ወቅትም አምባሳደር ሲራጅ   ኤምባሲው በናይሮቢ ከተማ ቢዝነስ ፎረም ለማዘጋጀት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዓላማውም የኬንያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስተዋወቅ  መሆኑን ተናግረዋል ።

የኬንያ የንግድ ምክርቤት የስራ ኃላፊዎች የሁለቱን ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስርን ለማጠናከር በጋራ መስራት ፍላጎት እንዳላቸውና በተለይም በተለያዩ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የሁለቱን ሀገራት ኩባንያዎች የሚያሳትፍ መድረክ የተሳካ ለማድረግ ከኤምባሲ ጋር እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

አምባሳደር ሲራጅም  ከንግድ ምክር ቤቱ ጋር ከዚህ በፊት ውጤታማ ስራ ለመስራት በመቻሉ  አመስግነው በቀጣይም ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰሩ  ገልጸዋል።

ከዚያም ባለፈ የሁለቱን ሀገራት የንግድ ምክር ቤቶችንም ለማስተሳሰር በቀጣይ  እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውንበኬንያ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.