Fana: At a Speed of Life!

የክርስትና እምነት ተከታዮች የገና በአል ሲያከብሩ በመረዳዳት እና የሌለውን በመደገፍ ሊሆን ይገባል- የደቡብ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድሮች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የክርስትና እምነት ተከታዮች መጭውን የገና በአል ሲያከብሩ በመረዳዳት እና የሌለውን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ የደቡብ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርሳነ መስተዳድሮች ገለጹ።
ምክትል ርሳነ መስተዳድሮቹ ከፋናብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ በበአሉ ወቅትም ህብረተሰቡ የኮሮና ቫይረስ ጥንቃቄዎችንም መዘንጋት እንደሌለበትም አሳስበዋል።
የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድረ አቶ ርስቱ ይርዳው ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ÷ በኢትዮጵያ በርካቶች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የህብረተሰቡን ድጋፍ የሚፈልጉ በርካቶች ናቸው ብለዋል።
ስለሆነም የእምነቱ ተከታዮች በአሉን ሲያከብሩ የተፈናቀሉትን እና ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን በመደገፍ ከጎናቸው በመሆን ማሳለፍ ይገባል ነው ያሉት።
የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያዊ የመደጋገፍ ባህልን በበአሉ ማሳየት እና ድጋፍ ለሚሹትም ከጎናቸው መሆንን ይጠይቃል ነው ያሉት።
የክርስትና እምነት ተከታዮችም ከዚህ ቀደም ሲያደርጉት የነበረውን ድጋፍ በገና በዓልም ማድረግ እና የተቸገሩትን በመርዳት ማሳለፍ ይገባል ብለዋል።
በአሉን ሲከበር ትልቅ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሮቹ እንደከዚህ ቀደሙ መሰባሰብ የማይቻልበት ጊዜ በመሆኑ ህብረተሰቡ በአሉን ሲያከብር ለኮሮና ቫይረስ የሚያስፈልጉ ጥንቃቄዎችን በመተግበር ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።
በአሉን በመረዳዳት ማሳለፉ እንዳለ ሆኖ አሁን ለአለምም ሆነ ለኢትዮጵያ ትልቅ ስጋት የሆነው ኮሮና ግን መዘንጋት እንደሌለበት ምክትል ርሳነ መስተዳድሮቹ ተናግረዋል።
ለነገ መኖር የዛሬ ጥንቃቄ መሰረት ነው ያሉት ምክትል ርሳነ መስተዳድሮቹ ወረርሽኙ አሁን ካለበት የከፋ እንዳይሆንም ሁሉም ሀላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።
የደቡብ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
በዙፋን ካሳሁን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.