Fana: At a Speed of Life!

የኮምቦልቻ ሠመራ ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በየቀኑ በአማካይ 200 ሰዎች ሲሳተፉበት የቆየው የኮምቦልቻ ሠመራ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቆ የሙከራና የፍተሻ ሥራ እየተከናወነ ነው።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማከፋፈያ ጣቢያዎችና ማስተላለፊያ መስመሮች ኦፕሬሽን ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሀብታሙ ውቤ እንደገለፁት÷ በቡርቃና ካሳጊታ አካባቢ በሽብርተኛው የህወሓት ቡድን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ሙሉ በሙሉ ተጠግነዋል።
ድምፅና ዳታ ለማስተላለፍ ከተዘረጋው የኦፕቲካል ፋይበር ውጪ የጥገና ሥራው በመጠናቀቁ÷ ከኮምቦልቻ ሠመራ በተዘረጋው መስመር ኃይል ሲያገኙ የነበሩ የአፋር ከተሞች በሙሉ ኃይል እንዲያገኙ መስመሮችን ዝግጁ ለማድረግ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል የፍተሻ ሥራ ተከናውኗል ብለዋል።
በዛሬው ዕለት የሰመራ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል እንዲያገኝም ተደርጓል ነው ያሉት።
ይህን ተከትሎ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል ያሉት የሥርጭት መስመሮች ዝግጁ ሲሆን ሚሌ፣ ዲቼቶ፣ ሎጊያና ሰመራን ጨምሮ በርካታ የአፋር አካባቢዎች ኃይል የሚያገኙ ይሆናል ተብሏል።
በኮምቦልቻ ሠመራ መስመር በጥገና ሥራ ላይ በየቀኑ በአማካይ ከ200 ያላነሱ የቴክኒክ ባለሙያዎችና የጉልበት ሠራተኞች ሲሳተፉ ቆይተዋል።
የቀኑን ሐሩርና ውሃ ጥም ተቋቁመው እስከ ሁለት ወር ሊወስድ የሚችለውን ሥራ በሁለት ሳምንት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ላደረጉ የማከፋፈያ ጣቢያና የማስተላለፊያ መስመር የጥገና ባለሙያዎች እንዲሁም የራስ አቅም የጥገና ሰራተኞች አቶ ሀብታሙ ምስጋና ማቅረባቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.