Fana: At a Speed of Life!

የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በድንበር አካባቢዎች ቁጥጥር እንዲጠናከር ተደረጓል- አቶ ሙስጠፌ መሃመድ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በድንበር አካባቢች ቁጥጥር እንዲጠናከር መደረጉን የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ገለፁ።

ክልሉ ከጅቡቲ፤ ሶማሊያና ኬኒያ ጋር በድንበር እንዲሁም ከሶስቱ ሀገራት ህዝቦች ጋር ደግሞ በባህል እና አኗኗር ዜይቤም ይዛመዳል።

ምክትል ርዕስ መስተዳድሩ አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በስልክ በነበራቸው ቆይታ፥ የአጎራባች ሀገራት አርብቶ አደሮች አብዛኛውቹ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ በመሆኑ የመከላከል ስራው ፈታኝ ያደርገዋል ብለዋል።

ሆኖም ግን ተጋላጭነቱና ፈተናው ከፍተኛ ቢሆንም ክልሉ የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር እየሰራ ይገኛል ሲሉም አስታውቅዋል።

የክልሉ ተጋላጭነት አሁንም ከፍተኛ መሆኑን የሚያነሱት ምክትል ርዕስ መስተዳድሩ፥ በተለይም በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ያለው ሁኔታ አስደንጋጭ መሆኑ አንስተዋል።

ያለውንም አሳስቢ ሁኔታ ከፌደራል መንግስት የሚመለከታቸው አካላት ጋር መረጃ ልውውጥ ስለመደረጉን ተጨማሪ ዝግጅት በማስፈለጉም አሁንም አስፍላጊው ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አቶ ሙስጠፌ አስታውቀዋል።

በሁሉም ዘርፍ አቅምን ለማጎልበት ከሚደረገው ጥረት በተጨማሪም ድንበር ተሻግረው የሚመጤ ዜጎች ወደ ህብረተሳቡ እንዳይቀላቀሉ እየተደረገ መሆኑንም ገልፀዋል።

በዚህም ከአጎራባች ሃገራት በተለያየ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ በሚገቡ ከ1 ሺህ 500 በላይ ዜጎች በአስገዳጅ ለይቶ ማቆይ እንዲገቡ በማድረግ ክትትል እየተደረገላቸው ነው።

በተጨማሪም በክልሉ በደወሌ፤ ቶጎ ውጫሌ፤ ቦህ እና ሞያሌ በኩል ጥበቅ ቁጥጥር በማድረግ ድንበር ተሻግረው የሚገቡ ዜጎች የሚቆዩበት አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ተዘጋጅተዋል።

በቀጣይ ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ዜጎች እንዳሉ መረጃ በማመላከቱ በደወሌ፣ ቶጎ ውጫሌ፣ ቦህ እና ሞያሌ ድንበር አካባቢዎቹ ቁጥጥሩ እንዲጠናከር መደረጉን አስታውቅዋል።

ለዚህም የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ማዕከላትን ወደ 15 በማሳደግ የምርመራ ማዕከልን ከአንድ ወደ ሶሰት የማሳደግ ስራ ተጅመሯል ብለዋል።

ከሰሞኑ ከአጎራባች ሀገራት በሚመጡ ኢትዮጵያዊያን ስራ በዝቶበት ከቆዩት አንዱ የድሬድዋ ከተማ አስተዳድር ይጠቀሳል።

በድሬደዋ ከተማ ከጅቡቲ በኩል ያለው ድንበር ቁጥጥር እየተጠናከረ በመምጣቱ አሁን ላይ ወደ ከተማዋ የሚገቡ ዜጎች ቁጥር ቀንሷል ነው ያሉት የከተማዋ ጤና ቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ለምለም በዛብህ።

የቫይረሱን ስርጭት ከመከላከል በተጨማሪ በሆቴሎች፣ በባንክ፣ በአውሮፕላን ማረፊያ እና በአገልግሎት ዘርፍ ለተማሩ የህብረተሰብ ክፍል ከትናትናው ዕለት ጀምሮ በፍቃድኝነት የምርመራ ስራ መጀመሩንም ገልፀዋል።

በበላይ ተስፋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.