Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወደ ተለያዩ የዓለም ሀገራት በመዛመት ላይ ይገኛል።

አሁን ላይም ቫይረሱ ከ156 በላይ በሆኑ የዓለም ሀገራት ውስጥ መስፋፋቱን የዓለም ጤና ድርጅት ያስታወቀ ሲሆን፥ በአፍሪካም ኢትዮጵያን ጨምሮ 26 ሀገራት ቫይረሱ እንድተገኘባቸው ተረጋግጧል፡፡

ካሳለፍነው ዓርብ ጀምሮ እስከ ትናንት በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አራት መድረሱን የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

ስለሆነም የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ማንኛውም ግለሰብ የሚከተሉትን ቅድመ ጥንቃቄዎች ሊያደርግ እንደሚገባ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።

  • ለእጅ ንጽህና መጠበቂያ የሚሰሩ አልኮል ነክ ምርቶችን መጠቀም
  • ባልታጠበ እጅ አይን፣ አፍንጫ እና አፍን አለመንካት
  • ቫይረሱ ሪፖርት ከተደረገባቸው ሀገራት የመጡ ተጓዦች ሆነው የበሽታውን ምልክት ከሚያሰዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ በተጫማሪም ከ1 እስከ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ
  • ስለቫይረሱ በቂ መረጃ በማግኘት መተግበር ፣

በቫይረሱ መያዛቸውን የተጠረጠሩ ሰዎች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች፦

  • ወደ ሀገር በተመለሱ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ የመተንፈሻ አካል ህመም፣ ትኩሳትና እንደሳል ያሉ የህመም ምልክቶች ካለብዎት ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት ማግኘት፣
  • የቫይረሱ ስሜት ከመፈጠሩ አስራ አራት ቀናት በፊት ቫይረሱን ሪፖርት ወዳደረጉ ሃገራት ሄደው ከነበረ ይህንንም ለጤና ባለሙያው ማስረዳት፤
  • በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ጊዜ ቫይረሱ ወደ ጤነኛሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ፣ በመሃረብ ወይም በሶፍት መሸፈን፣
  • አፍና አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ እና እጅን ሁልጊዜ በውሃና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል።
  • ቫይረሱን ሪፖርት ወዳዳረጉ ሀገራት ሄዶ የቫይረሱን ምልከቶች ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቋም ማሳወቅ ወይም ከታች በተገለፁት አድራሻዎች በመጠቀም ሪፖርት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።
  1. በነፃ የስልክ መስመር- 8335
  2. በመደበኛ የስልክ ቁጥር -0118276796
  3. በኢሜል አድራሻ ephieoc@gmail.com
  4. ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
    https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.