Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ”ማስክ ኢትዮጵያ” ዘመቻ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ በዓለም የጤና ድርጅት የተጀመረውን የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛን የሚያስተዋውቀውን ዘመቻ መቀላቀሏን አስታወቁ፡፡
 
ዘመቻውን “ማስክ ኢትዮጵያ” በሚል መቀላቀሏን አስታውቀዋል፡፡
 
በዚህ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ዘመቻ የሁላችንም ተሳትፎ ጨምሮ፣ እውቀታችን አድጎ፣ ባህሪያችንም ተለውጦ፣ ወረርሽኙን በተሻለ አቅም መከላከል እንችላለን ብዬ አምናለሁ ብለዋልፕሬዚዳንቷ፡፡
 
እንዲሁም ሁላችንም የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛን በብዛት በማምረት፣ በትክክል በመጠቀም፣ ራሳችንንም፣ ወገኖቻችንንም ከበሽታ እንጠብቅ ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
 
አንድም ሰው በበሽታ እንዲያዝ ፣ የማይተካ ሕይወት እንዲያልፍ ፣ የሃገራችን እድገት እንዲስተጓጎል ምክንያት አንሁን፣ የሁላችንም ያልተቋረጠና የተባበረ ጥረት ወረርሽኙን ለማሸነፍ ይሁን ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
 
መረጃው የፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ነው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.