Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያገለግሉ የህክምና ግብዓቶች ስርጭት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከል የሚያገለግሉ የተለያዩ የህክምና መገልገያ ግብዓቶች ስርጭት መጀመሩን የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው የመደበኛ ኘሮግራም ባለሙያ አቶ አገኘው ናደው እንደገለጹት፥ ለኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከል የሚያገለግሉ የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ስርጭት በትናንትናው ዕለት ተካሂዷል።

በዚህ መሰረት ኤጀንሲው 16 አልጋዎች፣ 12 ሺህ 640 የፊት መከለያ (ማስክ)፣ 1 ሺህ ቦቲ ጫማ፣ 40 ካኑላ፣ 600 ዴክስትሮስ ኖርማል ሣላይን፣ ኦ.አር.ኤስ 2 ሺህ 400 ሣኬት እና 100 ኢላስቲክ ባንዴጅ ለህብረተሠብ ጤና ኢንስቲቲዩት ማስረከቡን አስታውቋል።

እንዲሁም 20 ሠርጂካል ጎዝ፣ 23 ኤኘሮን ኘላስቲክ ኘሮቴክሽ እና ባለ አንድ ሺህ ሺ 50 የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶችን ለኢንስቲቲዩቱ መሰጠታቸው ተገልጿል።

የሕክምና መገልገያ ግብዓቶቹ ለቫይረሱ ቅድመ መከላከል ምርመራ ከማገልገላቸው ባለፈ ተያያዥ በሽታዎች ቢገኙ ሕክምና ለመስጠት የሚያገለግሉ መሆኑን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.