Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ፍቱን መፍትሄ ላይኖር ይችላል- የአለም ጤና ድርጅት

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ፍቱን መፍትሄ ላይኖር እንደሚችል የአለም ጤና ድርጅት አሳሰበ።
 
የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በበይነ መረብ በሰጡት መግለጫ ለቫይረሱ በአሁን ወቅት ፍቱን መፍትሄ የለም ወደፊትም ላይኖር ይችላል በማለት ተናግረዋል።
 
ይህ ሀሳብ የመጣው ድርጅቱ የኮሮና ቫይረስ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል ሲል ካስጠናቀቀ በኋላ ነው።
 
ሆኖም በዓለም እየተካሄደ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ሙከራ ቫይረሱን ለመከላከል ሊረዳ ይችላል ሲል ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል።
 
የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በሙከራ ላይ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ክትባት በሽታ የመከላከል አቅምን ያሻሽላል ሲል ማሳወቁ የሚታወስ ነው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.