Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ቢጨምርም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ተጠቃሚዎች ቁጥር ማሽቆልቆሉን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ቢጨምርም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ተጠቃሚዎች ቁጥር ማሽቆልቆሉን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ።
የኮሮናቫይረስ ከሚመረመሩ ዜጎች ውስጥ ከ10 በመቶ በላይ ቫይረሱ እየተገኘባቸው መሆኑን የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በጤና ሚኒስቴር በጋራ የተዘጋጀ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት ያለመ “እንድናገለግልዎ ማስክ ያድርጉ” ዘመቻ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ነው።
በማስጀመሪያ ዝግጅቱ ላይ የፌዴራል እና የአዲስ አበባ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ምርምራ ከሚደረግላቸው ከ10 በመቶ በላይ በሚሆኑት ቫይረሱ እየተገኘባቸው መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልፀዋል።
የበሽታው ስርጭት ቢጨምርም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ተጠቃሚዎች ቁጥር ማሽቆልቆሉን ተናግረዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.