Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ-19 ክትባት ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በአፍሪካ እንደሚሰጥ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በኦክስፎርድ የተመረቱ ሁለት የኮቪድ-19 ክትባቶች ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ በአፍሪካ ሊሰጡ እንደሚችሉ ተገለፀ፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በኮቫክስ እቅድ አማካኝነት ክትባቶቹን ወደ አፍሪካ ሀገራት የሚላኩበትን መንገድ ምቹ በማድረግ ለአስቸኳይ አገልግሎት እንዲውል ሁለት የኦክስፎርድ አስትራዜኒካ የኮቪድ -19 ክትባቶችን አጽድቋል ፡፡

ኮቫክስ የአለም ሀገራት ፍትሃዊ እና ውጤታማ የሆነ ክትባት እንዲያገኙና ተያያዥ ጉዳዮችን ለመደገፍ ሀብታቸውን የሚያሰባስቡበት ነው ፡፡

የአለም ጤና ድርጅት ረዳት ዋና ዳይሬክተር ማሪያንጌላ ሲማኦ “ክትባት የማግኘት አቅም የሌላቸው ሀገራት የጤና ሰራተኞቻቸውን እና ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ አካላትን ይከትባሉ” ብለዋል ፡፡

ክትባቱ 63 በመቶ ውጤታማ መሆኑ የተረጋገጠ ነው ብሏል ድርጅቱ ፡፡

የክትባት ባለሙያዎች ቡድን ክትባቱ ከ18 ዓመት በላይ ለሆናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ይሰጣል ብሏል፡፡

ክትባቶቹ የተመረቱት በደቡብ ኮሪያ አስትራዜኔካ-ስኪቢዮ እና በሕንድ ሴረም ኢንስቲትዩት ነው ፡፡

ደቡብ አፍሪካ ባለፈው ሳምንት የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት መስጠት ማቆሟ የሚታወስ ሲሆን፤ አዲሱን የኮቪድ-19 ዝርያ የመከላከል አቅሙ ዝቅተኛ ነው ስትል እንደምክንያትነት አስቀምጣለች፡፡

ሆኖም ባለሙያዎቹ ክትባቱ ከበድ ያሉ ጉዳቶችን ለመከላከል ውጤታማ እንደሚሆን ገልጸዋል ፡፡

እስካሁን በአህጉሪቱ ከ3 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፤ ከ98 ሺህ በላይ ሰዎችን ለህልፈት ዳርጓል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.