Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የመከላከል እና የመቆጣጠር ሥራዎችን ዳግም ትኩረት ተሰጥቶ በቅንጅት መሥራት ያስፈልጋል – ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የመከላከል እና የመቆጣጠር ሥራዎችን ዳግም ትኩረት ተሰጥቶ በቅንጅት መሥራት እንደሚያስፈልግ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።
አሁን ላይ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እየጨመረ ሲሆን፣ በአንጻሩ ደግሞ በሁሉም ደረጃ ቫይረሱን የመከላከል ትግበራው ስለተቀዛቀዘ እንዲሁም ፍጹም መዘናጋት ስለሚስተዋል ወረርሽኙ አሁንም የማኅበረሰቡ ስጋት ሆኖ መቀጠሉን ገልጸዋል።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝን የመከላከል ሥራዎችን ዳግም ለማጠናከር እና በቀጣይ የታቀደውን ሃገር አቀፍ ንቅናቄ በውጤታማነት ለመምራት የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ወቅት በየደረጃው የሚገኙ የሥራ ሃላፊዎች ትኩረት ሰጥተው ሥራውን እንዲሠሩ እና ኅብረተሰቡን ከወረረሽኙ እንዲታደጉ አቶ ደመቀ ማሳሰባቸውን ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.