Fana: At a Speed of Life!

የኮቪድ19 መከላከያ እርምጃዎች እና የህግ ተጠያቂነት የተከለከሉ ተግባራት

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስቴር የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ወቅታዊ ሁኔታ እና ኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር በወጣው መመሪያ 30 አፈጻጸም እንዲሁም በህግ ተጠያቂነት እና በተከለከሉ ተግባራት ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
• የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ መሰራጨቱን ተከትሎ፣ የኮቪድ 19 ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን መመሪያ 30ን ሙሉ በሙሉ ስራ ላይ ለማዋል ከጤና ሚኒስቴር ፣ ሰላም ሚኒስቴር፣ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ ፌዴራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የተውጣጣ ግብረ ሃይል በማቋቋም ካለፈው ሳምንት ሰኞ ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እና ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል፡፡
• ይህም ንቅናቄ በተለይ በአዲስ አበባ በስፋት የተሄደበት ሲሆን አበረታታች ውጤት ተገኝቶበታል፡፡ ለዚህም እንደማሳያ የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል፡፡
o ህብረተሰቡ መመሪያውን ለመተግበር ከፍተኛ መነሳሳት ማሳየቱና ተባባሪ መሆኑን ማረጋገጡ
o ንቅናቄው ከፍተኛ የሆነ የመገናኛ ብዙሃን እና የአብዛኛው ሰው ትኩረት ማግኘቱ
o ብዙ ተቋማት አቅደውት የነበረውን የተለያዩ ዝግጅቶች በመመሪያው መሰረት ማሻሻላቸውና አልፎም አንዳንድ ተቋማት ዝግጅታቸውን ማራዘማችው
o በልዩ ሁኔታ መሰብሰብ የሚፈልጉ አካላትም፣ ጉዳያቸውን ለሚመለከተው ክፍል እየስታወቁ ፈቃድ በመጠየቅ ላይ መሆናቸው
o ብዙ ተቋማት አገልግሎት ለመስጠት ማስክ ማድረግን አስገዳጅ እያደረጉ መሆኑ
o አብዛኛው ተጽእኖ ፈጣሪ አመራሮችና ግለሰቦች ተምሳሌት ሆኖ ለህዝቡ መታየት እና መልእክት ማስተላለፍ መጀመራቸው ይጠቀሳሉ፡፡
እነዚህ ሁሉ መልካም ጅምሮች የሁሉም ሰው እና ተቋም ልማድ ሆነው መቀጠል ያለባቸው ሲሆኑ በዚህ አጋጣሚ ተባባሪ ለሆነው ማህበረሰብ፣ተቋማት እና ለህግ አስከባሪ አካላቱ ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡
• ይህ ሲባል፣ መመሪያውን ተግባራዊ የማድረጉ ስራ የሁሉንም ትብብር አግኝቷል ማለት ግን አይደለም፡፡
በአደባባይ ማስክ ሳይደርጉ መንቀሳቀስ እንደማይቻል ተደንግጎም፣ ማስክ ሳያደርጉ የሚዘዋወሩ፣ በቂ ርቀት ያልጠብቁ፣ ከተፈቀደው ቁጥር በላይ የሰዎች ስብስብ የያዙና እና ያለ ማስክ የተደርጉ ስብሰባዎች፣የተለያዩ ዝግጅቶች በሳምንቱ ወስጥ ተከናውነዋል፡፡
ከፍተኛ ጥግግት በየካፌዎች፣ ምግብ ቤቶች፣ መዝናኛ ስፍራዎች፣ትራንስፖርት፣ የእምነት ቦታዎች ተስተውለዋል፡፡
• ከህግ አስከባሪ አካላቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ባለፈው አንድ ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ፣ ከ47 ሺህ የሚበልጡ ሰዎች፣ ከ115 በላይ ተቋማት መመርያ 30ን ጥሰው በመገኘታቸው የተለያዩ የማስተማሪያ እርምጃዎች የተወሰደ ሲሆን 20 ግለሰቦችና 10 ተቋማት ጉዳያችው በህግ በመታየት ላይ ነው፡፡ ይህም ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን ከዚህ ሳምንት ጀምሮ በሌሎች ክልል ከተሞችም እና ከተማ አስተዳደሮች በስፋት የሚኬድበት ይሆናል፡፡
• መመሪያውን የምንተገብረው ለራሳችን መሆኑን በመገንዘብ ተቆጣጣሪና ጠባቂ እንደማያስፈልገን እያሳሰብኩ ህግ አስከባሪዎችን በማምለጥ ከቫይረሱ መሸሸግ እንደማይቻል ልንረዳው ይገባል፡፡
• በዚህ በያዝነው ሳምንት፣ የበሽታው ስርጭት በፍጥነት መጨመሩ የቀጠለ ሲሆን እስከ መጋቢት 28 ባለው የጽኑ ህሙማን ቁጠር 850 የደረሰ ሲሆን የማቾች ቁጠር ከ 3 ሺህ አልፏል! ከዚህ ችግር ለመውጣት የጀመርነውን አበረታች ንቅናቄ አጠናክሮ መቀጥል ያስፈልጋል፡፡
ለዚህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪዬን እያቀረብኩ የሚከተሉት ተግባራት መቶ በመቶ ወደስራ እንዲውሉ አሳስባለው፡፡
▪ በየደረጃው ያሉ አመራሮች፡ ያለማስክ እና በመመሪያ 30 ከተፈቀደው አሰራር ውጪ ማንኛው አይነት ስብስቦች ማድረግ ባስቸኳይ እንዲቆም፤
▪ ሆቴሎች፡ ከተፈቀደው የሰው ቁጠር በላይ ማንኛውም አይነት ስብሰባዎችና ማህበራዊ ዝግጆች እንዳያከናውኑ ፤
▪ ካፌዎችና መዝናኛ ስፍራዎች፡ በአንድ ጠረጴዛ ከ3 ሰው በላይ እንዳይቀመጥ እና በጤረጴዛዎች መካከል ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀት እንዲኖር ማድረግ፤
▪ የእምነት ተቋማት፡ ማስክ ማድረኝ አስገዳጅ እንዲያደርጉ እና አካላዊ እቀት እንዲያስጠብቁ ፤
▪ አሽከርካሪዎች፡ ማስክ ማድረግ አስገዳጅ እንዲያደርጉ፤
▪ በትምህርት ቤቶች፡ የማስክ አጠቃቀም እንዲሻሻል፤
▪ ማንኛውም ተቋም፡ ያለማስክ አግልግሎት እንዳይሰጥ፤
▪ የሴክተር መስራቤቶች፡ በስራቸው ያሉ ተጠሪ ወይም እውቅና የሰጧቸውን የተለያዩ ተቋማት እና አገልግሎት የሚሰጡ አካላትን የመቆጣጠር ንቅናቄ እንዲያጠናክሩ፤በተለይ በትራንስፖርት፣ ሆቴሎች፣ካፌዎች የመዝናኛ ስፍራዎች፣የንግድ ስፍራዎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የእምነት ተቋማት
▪ ተጽኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፡ አርአያ ሆነው እንዲገኙ ለተካታዮቻቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እንዲሰሩ
▪ በህብረተስቡ ውስጥ ያሉ የተለያዪ አደረጃጅት ( እንደ እድር፣ የወጣቶች ማህበራት፣የሞያ የማህበራት) በአከባቢያቸውና በሚወክሉት አባላት ላይ የማስተማር ስራ እንዲሰሩ
▪ የህግ አስከባሪ አካላት፡ ተምሳሌት እንዲሆኑ እና ህግ የማስከብር ንቅናቄውን በሁሉም ተቋማት (በመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ) እጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪዬን አቀርባለው፡፡
• ሁላችንም የድርሻችን እንወጣ፣ ዳግም ትኩረት ለኮቪድ19 ምላሽ በመስጠት ህዝባችን ከከፋ ጉዳት እናድን!
አመሰግናለሁ!
May be an image of 1 person and text
0
People Reached
91
Engagements
Boost Post
75
9 Comments
7 Shares
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.