Fana: At a Speed of Life!

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው አወቃቀር እንደ ሰው ልጅ አካል የበርካታ አካላት ድምር ውጤት ነው-ኢንጂነር አይሻ መሀመድ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌዲሪ ኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የህግ ማዕቀፍና አተገባበር ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ከባለ-ድርሻ አካላት ጋር  በሀዋሳ እያካሄደ ነው።

ውይይቱ “ውጤታማ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ለኢትዮጵያ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል  እየተካሄደ እንደሚገኝም ነው የተገለጸው።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር  ኢንጂነር አይሻ መሀመድ÷ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ግዙፍ ሃብት፣ ቴክኖሎጂ፣ ከፍተኛ የሰው ኃይልና እውቀት የሚጠቀም ዘርፍ መሆኑን ገልፀው   የኢትዮጵያን ብልፅግና እውን ለማድረግ የሚያስችልበት ዕድልም እጅግ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው አወቃቀር እንደ ሰው ልጅ አካል የበርካታ አካላት ድምር ውጤት እንደመሆኑ የኮንስትራክሽን ዘርፉም በርካታ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ነው ያሉት ሚኒስትሯ ÷ ሰውነታችን ወይንም አካላችን ጤናማ እንዲሆን እንደምንጨነቅ ሁሉ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ጤንነትም በእጅጉ ሊያሳስበን ይገባል ብለዋል።

ሚኒሰውትሯ አያይዘውም የኮንስትራክሽን ሴክተሩም በተቆጣጣሪ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ብርቱ ክትትል ድጋፍና ቁጥጥር መታከም ይኖርበታልም ሲሉ ገልፀዋል።

በንቅናቄው መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ  ፕሮፌሰር ፀጋዬ ምትኩ በበኩላቸው÷ የኮንስትራክሽን ስራዎቻችን ጥራትን የሀገር ሀብትንና የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን መሰረት አድርገው መከናወን ያለባቸው በመሆኑ ባለድርሻ አካላት የጋራ ትኩረት ሊያደርጉ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

የከተሞችን ዕድገት ለማረጋገጥም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው በትክክለኛ መስመር ላይ መጓዝ ይኖርበታል ሲሉ አክለዋል።

የኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ነገዎም ÷የዘርፉን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የኮንስትራክሽን የቁጥጥርና የህግ ማዕቀፎች ወሳኝ በመሆናቸው የጋራ አረዳድ ሊኖር እንደሚገባ ተናግረዋል።

የንቅናቄ መድረኩ የዘርፉ የ10ዓመትና የ5ዓመት መሪ ዕቅዶች ለትግበራ ዝግጁ በሆነበት ዋዜማ መካሄዱ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርም ተናግረዋል።

በኮንስትራክሽን ስራዎች ተቆጣጣሪ ባለስልጣን አዘጋጅነት እየተካሄደ ያለው  ይህ አገር አቀፍ ንቅናቄ የኮንስትራክሽን ዘርፉን በማነቃቃት ማነቆዎችን በመለየትና የመፍትሄ አቅጣጫ አስቀምጦ በተሻለ መነሳሳት ለመራመድ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል።

የንቅናቄ መድረኩ በተለያዩ ስድስት ከተሞች እንደሚካሄድ ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.