Fana: At a Speed of Life!

የኮንሶ ዞን በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ለሚገኙ እርሶ አደሮች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የኮንሶ ዞን አስተዳደር በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የበልግ ዝናብ በቂ ባለመሆኑ እና የመኸር ዝናብ በወቅቱ ባለመዝነቡ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው አርሶ አደሮች የእንሰሳት መኖ ድጋፍ አደረገ።

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በተከሰተው ችግር ጉዳት ለደረሰባቸው አርሶ አደሮች ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹ፥ በቦረና ህዝብ ላይ የደረሰው ችግር የእኛም ችግር ነው ብለዋል።

እንደ ዋና አስተዳዳሪው ገለጻ በድርቅ ለተጎዱ እንሰሳት፥ 18 የጭነት መኪና የእንሰሳት መኖ እና ሁለት ቦቲ ውሃ ድጋፍ አድርገዋል።

የኦሮሞ እና የኮንሶ ህዝቦች አንድ ናቸው ያሉት አቶ ዳዊት፥ አስደንጋጭ የሆነውን የእንሰሳትን ሞት ለማስቀረት የበኩላችንን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ አቶ አብዱራሀማን አብደላ እንደተናገሩት፥ ለቦረና ወንድም ህዝብ ድጋፍ በማድረግ ረገድ የኮንሶ ዞን የመጀመሪያ በመሆኑ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

የቦረና ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጃርሶ ቦሩ፥ “ለችግራችን ደርሳችሁ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረጋችሁ ወንድማማች ህዝብ መሆናችሁን በተግባር አሳይታችሁናል” ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.