Fana: At a Speed of Life!

የኮንሶ ዞን የሚሊሻ ሠራዊት አባላትን አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የኮንሶ ዞን ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የሚሊሻ አባላትን አስመረቀ፡፡
የኮንሶ ዞን ከዚህ ቀደምም የሀገርቱን ጸጥታ ለማስከበር በሚደረገው ተልዕኮ ሀብት በማሰባሰብና እስከ ግንባር ድረስ በመሄድ ከመከላከያ ሠራዊት ጎን በመቆም ያለውን ቁርጠኝነትና አጋርነት አሳይቷል ሲሉ የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ገረሱ ካታሌ ገልጸዋል፡፡
የዛሬ ተመራቂዎችም ከሀገሪቱና ከዞኑ የጸጥታ ኃይል ጋር በመቆም በአቅም ግንባታ፣ በሞራልና በስነልቦና ታጥቀው መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት፡፡
ተመራቂዎቹም ወደ ሥራ በሚሰማሩበት ወቅት ህገ ወጥ የመሳሪያ ዝውውር፣ የኮንትሮባንድ ንግድ መከላከልና ለጸጥታ አስጊ የሆኑ ጉዳዮችን የመለየት ኃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን ተናግረዋል።
የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በበኩላቸው÷ ተመራቂዎቹ ህገ መንግስቱን ለማስከበር ሀገራቸውን፣ ህዝቡንና ህገ መንግስቱን በመውደድ ከሌሎች ጸጥታ ኃይሎች ጎን በመቆም የሀገርን፣ የዞኑና የአከባቢያቸውን የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተጣለባቸውን አደራ በጽናት እንዲወጡም ጭምር የስራ መመሪያ መስጠታቸውን ከደቡብ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.