Fana: At a Speed of Life!

የኮይሻ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫን ከብሄራዊ የሃይል ቋት ጋር ለማገናኘት የ500 ሚሊየን ዮሮ የብድር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከላርሰንና ቱቡሮ ሊሚትድ ከተሰኘ ኩባንያ ጋር የ500 ሚሊየን ዮሮ ብድርና የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
 
ስምምነቱን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ ከላርሰን እና ቱብሮ ሊሚትድ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተፈራርመዋል፡፡
 
ስምምነቱ ለ15 ዓመታት የሚቆይ ሲሆን ክፍያው በአነስተኛ ወለድ የሚከፈል ነው ተብሏል፡፡
 
ገንዘቡ የሚውለው የኮይሻ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫን ከብሄራዊ የሃይል ቋት ለማገናኘት፣ የኤሌክትሪክ መስመር ማስተላለፊያና ለንዑስ ጣቢያ ፕሮጀክት ግንባታ እንዲሁም ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ዕጥረት በሚገኝባቸው በምስራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ያለውን ችግር ለመቅረፍ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል
 
ዋና መስሪያ ቤቱን ህንድ ሙባይ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው ይህ ኩባንያ በግሉ ዘርፍ ከተሰማሩ የህንድ ኩባንያዎች ትልቁና ተቀባይነት ያለው፡፡
 
የ80 ዓመታት ልምድን ያከበተው ከላርሰንና ቱቡሮ ሊሚትድ በቴክኖሎጂ፣ በኢንጅነሪንግ ፣ በግንባታ እና በማምረቻው ዘርፍ ከፍ ያለ አቅም የፈጠረ ነው ተብሏል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.