Fana: At a Speed of Life!

የኮይሻ ፕሮጀክት የዓለም አቀፍ የቱሪዝም ስበትን እንደሚጨምር ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮይሻ ፕሮጀክት የዓለም አቀፍ የቱሪዝም ስበትን የሚጨምርና የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ መሆኑን የደቡብ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ገለፀ፡፡
የዓለም የቱሪዝም ቀን በደቡብ ክልል ደረጃ በዳውሮ ዞን እና በኮንታ ልዩ ወረዳ እየተከበረ ነው፡፡
የደቡብ ክልል ባህል፣ ቱሪዝም ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይለማርያም ተስፋዬ እንዳሉት፥ ከጊቤ 3 እስከ ጊቤ 4 ያሉትን አጠቃሎ የሚይዝ እና ለፕሮጀክቱ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ ስራ እየተከናወነ ነው፡፡
ቀኑን አስመልክቶ ባለፋት ሁለት ቀናት በዳውሮና በኮንታ የሚገኙ ሀብቶች፣ የኃላላ የድንጋይ ካብ፣ የጊቤ ሶስት የሀይል ማመንጫ ግድብ፣ የኦሞ ወንዝ ሰው ሰራሽ ሀይቅ፣ የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክ፣ እንዲሁም ሌሎች የቱሪዝም ሀብቶች ተጎብኝተዋል።
በዚህ ወቅት የጨበራ ጩርጩራ ብሔራዊ ፓርክን ለማልማት የመንገድ ልማት ስራዎችን ጨምሮ ሌሎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎች በመከናወን ላይ እንደሚገኙም በጎብኝቱ ወቅት ተነግሯል።
ከጉብኝቱ በኋላም በኮንታ ልዩ ወረዳ የፖናል ውይይት የተካሄደ ሲሆን በቀጣይም በቱሪዝሙ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ይካሄዳል ተብሏል፡፡
በዓሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ በክልል ደረጃ ለ26ኛ ጊዜ ቱሪዝም ለገጠር ልማት በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡
በብርሃኑ በጋሻው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.