Fana: At a Speed of Life!

የወላይታ ሶዶ የመርካቶ ገበያ ማዕከል ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለተጠቃሚዎች ይተላለፋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ሶዶ ከተማ በዘመናዊ መልክ እየተገነባ የሚገኘው የመርካቶ ገበያ ማዕከል በታቀደው የጊዜ ገደብ ባለመጠናቀቁ በነዋሪች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መርክነህ ማለዳ ÷በዘመናዊ ሁኔታ እየተገነባ የሚገኘው የመርካቶ ገበያ ማዕከል የመልሶ ግንባታ ሥራው ያለበት ደረጃ ተፈትሾ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለተጠቃሚዎች ይተላለፋል ብለዋል፡፡
ባለፈው ዓመት በእሳት አደጋ የወደመው የመርካቶ ገበያ ማዕከል በዘመናዊ መንገድ መልሶ ለመገንባት ታቅዶ እየተሰራ ቢሆንም÷ የተጀመረው ስራ በመጓተቱ ተቸግረናል ሲሉ ከአሁን ቀደም በመርካቶ ገበያ የሚነግዱ የህብረተሰብ ክፍሎች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል ።
የገበያ ማዕከሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ አለመጠናቀቅ ለሥራ ማጣትና መሰል ችግሮች እንደዳረጋቸው ጠቁመው÷ የገበያ ማዕከሉ በርካታ ዜጎች ሰርተው የሚተዳደሩበት ከዕለት ተዕለት ህይወታቸው ጋር የተቆራኘ በመሆኑ በአፋጣኝ ግንባታው ተጠናቆ ወደ ስራ እንዲገባ ጠይቀዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ጣቢያችን በሰራው ዘገባ በአራት ወር ጊዜ ገደብ ተጠናቆ ወደስራ ይገባል መባሉ የሚታወስ ሲሆን÷ አሁንም ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የቅሬታ አቅራቢዎችን ሀሰብ መነሻ በማድረግ ባደረገው ቅኝት÷ የገበያ ማዕከሉ ግንባታ መጓቱትን አረጋግጧል፡፡
የሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መርክነህ ማለዳ በሰጡት ምላሽ÷ የመርካቶ ገበያ ማዕከል ግንባታ በተያዘው የጊዜ ገደብ በተለያየ ምክንያት አለመጠናቀቁን ገልጸው÷ የመልሶ ግንባታ ሥራው ያለበት ደረጃ ተፈትሾ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለተጠቃሚዎች ይተላለፋል ብለዋል፡፡
የመርካቶ ገበያ ከአሁን በፊት ለ5 ጊዜያት የእሳት አደጋ እንደደረሰበት ያነሱት ከንቲባው÷ ባለፈው ዓመት ታህሳስ ወር ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ እጅግ ከፍተኛ ውድመት አስከትሎ ማለፋን አስታውሰዋል።
በመሆኑም በተደጋጋሚ የሚደርሰውን የእሳት አደጋ ለመከላከል በተወሰደው እርምጃ የገበያ ማዕከሉ በዘመናዊ ሁኔታ እየተገነባ እንደሆነ አንስተዋል።
በማስተዋል አሰፋ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.