Fana: At a Speed of Life!

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሰራዊት የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሰራዊት 45 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የአይነት እና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ዩኒቨርሲቲው÷ 1መቶ ኩንታል ስኳር፣ 1መቶ ኩንታል ጤፍ ፣ 50 ዘመናዊ አልጋ ፣ 200 ብርድልብስ እና 40 ሰንጋ በአጠቃላይ 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በማውጣት ነው ድጋፍ ያደረገው፡፡

በተጨማሪም ከአስተዳደሩ እንዲሁም ከሰራተኞች 39 ሚሊየን ብር በመሰብሰብ ድጋፍ አድርጓል መባሉን ከመከላከያ ሰራዊት የፌስቡክ ገጽ ያኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ÷ ዜጎችን በትምህርት መቅረፅ የሚቻለው ሀገር ሰላም ስትሆን በመሆኑ ከዚህ በፊት በነበሩ ዙሮችም ሆነ ዛሬ ሀገርን ለማዳን የህልውና ዘመቻ ላይ ለሚገኘው ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ዩኒቨርሲቲያችን ደጀንነቱን በማሳየቱ እጅግ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።

የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሉዊጂ በበኩላቸው÷ ለመከላከያ ሰራዊት አጋርነቱን በተግባር በማሳየት አስተዋጽኦ እያበረከተ ለሚገኘው ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.