Fana: At a Speed of Life!

የወሎን ሰላም ለመጠበቅ የሀይማኖት ተቋማት ሚና የጎላ ነው ተባለ

 

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) – የሀይማኖት መቻቻል ተምሳሌት የሆነችውን ወሎ ሠላሟን ለማደፍረስ የሚሞክሩ ሀይሎችን ነቅቶ ለመጠበቅ የሀይማኖት ተቋማት ሚና የጎላ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን የሀይማኖት ተቋማት ፎረም ውይይት ባካሄደበት ወቅት፣ የሀይማኖት መሪዎቹ እስካሁን የተጠበቀውን የዞኑን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ ከመንግስት ጋር በመቀናጀት የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ  ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የሰበካ ጉባዔ ክፍል ሀላፊ  ሊቀስዩማን ስነ-ፀሐይ አድማሴ ፥ የእምነት ልዩነትን እንደ ምክንያት በማድረግ ህብረተሰቡን ለመከፋፈል የሚጥሩ የእኩይ አስተሳሰብ  ምልክቶችን በጊዜ ማረም ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የደቡብ ወሎ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ሰብሳቢና የሀይማኖት ተቋማት ፎረሙ ም/ሰብሳቢ ሸህ ሰይድ ዘይን ያሲን በበኩላቸው ለራሱ ሰላም መሆንን የሚሻ ሁሉ ስለሌሎች ሰላም መሆን ሊያስብ ይገባል ብለዋል፡፡

በመካነ እየሱስ የማእከላዊ ሲኖዶስ ወንጌል መምሪያ ኃላፊ  ቄስ ሙሉጌታ አለሙ፥ በወንድማማቾች መካከል ጠብን የሚዘሩ የእምነቱ አስተምህሮ አጥብቆ እንደሚኮንናቸውና ሰላምን መጠበቅ ከሁሉም የሚጠበቅ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን አንስተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰይድ መሀመድ፥ ዞኑ በአንፃራዊነት ሰላሙን ጠብቆ እንዲቆይ ያደረጉት የህዝቡ ሰላም ወዳድነት፣ የሀይማኖቶች መልካም አስተምህሮና የፀጥታ አካላት  ከአመራሩ ጋር የነበረው ቅንጅት መሆኑን በምክንያትነት አንስተዋል፡፡

በአንድነት  ናሁሰናይ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.