Fana: At a Speed of Life!

ለወንጪ፣ ጎርጎራና ኮይሻ ፕሮጀክቶች ግንባታ የኦሮሚያ ክልል 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር አሰባሰ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሸገር ፕሮጀክት ቀጣይ ምዕራፍ ለሆነው የወንጪ የጎርጎራ እና ኮይሻ ፕሮጀክቶች ግንባታ የሚውል የገበታ ለሀገር የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልል አዘጋጅነት ተካሂዷል።

በፕሮግራሙ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሀብቶች ተገኝተዋል።
በዝግጅቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ለፕሮጀክቱ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ማሰባሰቡ ይፋ ሆኗል ።

በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ እንዳሉት÷ እንደ ሀገር የተገነቡ የእንጦጦ እና መሰል ፕሮጀክቶች መጨረስ እንደምንችል አመላካች በመሆናቸው የክልሉ መንግስት ከክልሉ ባላሃብቶችና ህዝቡ ጋር በመሆን የገበታ ለሀገር የመክፈቻ ፕሮግራም ማዘጋጀቱን ገልፀዋል።

የወንጪ ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር ዶክተር አብርሀም በላይ በበኩላቸው የወንጪ ፕሮጀክት ወንጪን እና ደንዲን ሀይቆች በጋራ የሚያለማ መሆኑን ገልፀዋል።

በትዝታ ደሳለኝ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.