Fana: At a Speed of Life!

የወገን ጥምር ጦር የፀረ ማጥቃት ርምጃ፣ ወራሪውን መንጋ መውጫ መግቢያ እያሳጣው ነው – የኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀግናው የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት የአማራ ልዩ ኃይል ፋኖና ሚሊሺያ በወሎ ግንባር በወረባቦ፣ በተሁለደሬ፣ ኩታበርና ደላንታ በወሰዱት የፀረ ማጥቃት ርምጃ በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ እያደረሱ መሆናቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፥ ጠላት በወረባቦ፣ በተሁለደሬ፣ ኩታበርና ደላንታ አካባቢዎች ያሰለፈው ኃይል ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።

ከጥቃቱ የተረፈውም እግሬ አውጪኝ በማለት እየፈረጠጠ ይገኛል።

ጠላት ያሰለፈው መንጋ ይዞት የመጣው መሣሪያ ገሚሱ ከጥቅም ውጭ ሲደረግ ገሚሱ ተማርኳል።

የጸጥታ ኃይላችን በወራሪው የሽብር መንጋ ላይ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ ኪሳራ በመሸሽ በየሸጡ፣ በየወንዙና በየጋራው እየተሽሎከሎከ የሚገኘውን የተበታተነ የጁንታ መንጋ፣ የየአካባቢው ሚሊሺያና አርሶ አደር ተደራጅቶ በመከታተል፣ የሀገር ደጀንነቱን ሊያጠናክር ይገባል።

እስካሁንም ከጀግናው የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት ጎን የቆመው የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሺያ ከየአካባቢዎቹ ነዋሪ ጋር እየፈጸመው የሚገኘው አኩሪ የጦር ሜዳ ገድል ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በመግለጫው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.