Fana: At a Speed of Life!

የወጪ ንግዱን በማጠናከር የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የወጪ ንግዱን በማጠናከር የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ማሳደግ እንደሚያስፈልግ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለወጪ ንግድ ማነቆ በሆኑ ችግሮችና  እና መፍትሄዎች  ዙሪያ  ከአምራቾች፣ ላኪዎችና ከሚመለከታቸው የመንግስት እና መንግስታዊ ካልሆኑ  አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ነው።

ውይይቱ በተለይም በአምራች ኢንዱስትሪው የወጪ ንግድ ላይ ያሉ ችግሮች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

በመድረኩ  ላይ ተገኙት የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሄር ÷ የሃገሪቱ የወጪ ንግድ በሚፈለገው መጠን እያደገ አይደለም ብለዋል።

የወጪ ንግዱን በማጠናከር የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ማሳደግ ያስፈልጋልም ብለዋል ሚኒስትሯ።

የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የጂቡቲ ወደብ አገልግሎት ክፍያ ከፍተኛ መሆን፡ የፋይናንስ እጥረት፡ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት እጥረት እና ሌሎች ችግሮች ለዘርፉ  እድገት ማነቆ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

የንግድ እናኢንዱስትሪ ሚኒስቴርም ዘርፉን ለማሳደግ ለኢንዱስትሪው የተሻለ ሁኔታ በመፍጠር፣ የውጭ ባለሃብቱን በመሳብ እና አምራቾች የወጪ ንግዱ ላይ እንዲሳትፉ ድጋፍ በማድረግ ላይ ትኩረቱን አድርጎ እየስራ  መሆኑም ተገልጿል፡፡

በሃይማኖት ኢያሱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.