Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ኢንቨስተሮች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት የተቋቋመው የቅንጅት መድረክ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)የውጭ ኢንቨስተሮች የሚያጋጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት የተቋቋመው የቅንጅት መድረክ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ፡፡

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና በጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ ሚኒስትር አምባሰደር ግርማ ብሩ የሚመራው የቅንጅት መድረክ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።

በስብሰባው የውጭ ባለሀብቶች በአገራችን እያደረጉ ባለው የኢንቨስትመንት እንቅስቀሴ እያገጠሙ ያሉ ችግሮች በዝርዝር ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ውይይቱን ተከትሎም በቀጣይ መሰራት በሚገባቸው ስራዎች ላይ አቅጣጫ መቀመጡን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የቅንጅት መድረኩ ታህሳስ 23/ 2012 ዓም በተደረገው የመጀመሪያ ስብሰባ ከዚህ በፊት የነበረውን የቅንጅት መድረክ እንደገና ለማስጀመር እና የውጭ ባለሀብቶችን ችግር በቅርበት በመከታተል መፍትሄ ለማፈላለግ እንዲቻል መቋቀሙ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.