Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ከአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ቲቦር ናዥ ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ጋር በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ የስልክ ውይይት አካሄዱ።
 
የውጭ ጉዳይ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት በትግራይ ክልል እያካሄደ ስለሚገኘው ዘመቻ ለቲቦር ናዥ ገለፃ አድርገዋል።
 
የህወሃት ወታደራዊ አቅም ሲጠፋ ፣ ጥቃት የተፈፀመባቸውን የመከላከያ ሰራዊት አባላት ነፃ ሲወጡ እና በክልሉ የህግ የበላይነት ሲረጋገጥ ዘመቻው እንደሚያበቃ ለአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
 
እንዲሁም በትግራይ ክልል መንግስት ስላወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ከአዋጁ ጋር ስለተያያዙ ስራዎችም ገለፃ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ቲቦር ናዥ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ሰላም በቀጠናው ሰላምን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በስኬት በመጠናቀቁም ለቲቦር ናዥ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.