Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ከፍተኛ አማካሪ ምክር ቤት የስራ አስፈጻሚ አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ከፍተኛ አማካሪ ምክር ቤት የስራ አስፈጻሚ አባላት ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከስራ አስፈጻሚ አባላቱ ጋር በኮቪድ-19 እና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ነው የቪዲዮ ኮንፈረንስ ውይይት ያደረጉት፡፡

በውይይቱም ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ፣ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሂደትና ግድቡን ለማጠናቀቅ ከዳያስፖራው ስለሚጠበቁ ተግባራት እንዲሁም ዳያስፖራው አስተዋጽኦ ሊያደርግባቸው ስለሚገቡ ልዩ ልዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ምክክር መደረጉን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ አባላት በተጨማሪ በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አቶ ፍጹም አረጋና የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.